የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከኮስታሪካ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከኮስታሪካ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ያዘጋጀው የ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር በቱርኪዬ መካሄዱን ቀጥሏል።
በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል።
ብሔራዊ ቡድኑ ሁለተኛ ጨዋታውን ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 ላይ ከኮስታሪካ ጋር ያደርጋል።
በምድብ ሁለት የምትገኘው ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ዩራጓይን 3 ለ 0 አሸንፋለች። ሕዳት ካሱ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።
ኮስታሪካ በመጀመሪያው ጨዋታ በኖርዌይ 4 ለ 1 ተሸንፋለች።
በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የሚመራው ቡድን ጨዋታውን ካሸነፈ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያልፋል።
በምድብ ሁለት ሌላኛው መርሐ ግብር ኖርዌይ ከዩራጓይ ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
በምድብ አንድ ቱርኪዬ ከኡዝቤኪስታን፣ ሞሮኮ ከፓራጓይ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በተያያዘም በውድድሩ ላይ እየተሳተፋ የሚገኘው ከ18 ዓመት በታች የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በፀረ አበረታች ቅመሞች እና በጨዋታ ማጭበርበር ዙሪያ ስልጠና መውሰዱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።