ቀጥታ፡

ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሩክ ሰሙ እና አንተነህ ተፈራ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አንተነህ ተፈራ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል። 

ቢንያም አይተን በፍጹም ቅጣት ምት ለአዳማ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ባህር ዳር ከተማ በ35 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ  በ33 ነጥብ ከነበረበት 9ኛ ወደ 10ኛ ዝቅ ብሏል።

አዳማ ከተማ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም