ቀጥታ፡

የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018(ኢዜአ)፡-የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ አብያተ ክርስትያናት እና አድባራት እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሃይማኖት አባቶች እና ምዕምናን በተገኙበት የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየታሰበ ነው።


 

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና ሌሎች ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

ኢየሱስ ክርስቶስ በስቅለቱ ለሰው ልጆች ፍጹም ፍቅርን፣ ትህትናንና ይቅርታን አስተምሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም