ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ንዲያሺሚዬ ሽኝት አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ንዲያሺሚዬ ሽኝት አደረጉ
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ሽኝት አድርገዋል።
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።