ቀጥታ፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 14 ነጥብ 86 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ፕሮጀክቶች ፈቃድ ወስደዋል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፡- በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት14 ነጥብ 86 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 221 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ፈቃድ የተሰጠባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎችም 90 በግብርና፣ 72 በአገልግሎት እንዲሁም 59 በኢንዱስትሪ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር) ለኢዜአ አስረድተዋል።

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ካወጡት ፕሮጀክቶች መካከል 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡት 34 ዳያስፖራ ባለሃብቶች መሆናቸውንም አመላክተዋል።

በአጠቃላይ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያወጡት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ለ33 ሺህ 885 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠሩም ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በዘጠኝ ወራት ወደ 9 ቢሊየን 445 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ካፒታል ያስመዘገቡ 106 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መስፈርቱን አሟልተው የጠየቁት መሬት ተላልፎላቸው ወደ ተግባር እንዲገቡ በክልሉ መንግሥት ውሳኔ መሰጠቱንም አንስተዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ #ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም