የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ዛሬ በ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይመለሳል።
ምሽት አራት ሰዓት ላይ ዌስትሃም ዩናይትድ ከዎልቭስ በለንደን ስታዲየም ይጫወታሉ።
ዌስትሃም ዩናይትድ በ29 ነጥብ 18ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ተጋጣሚው ዎልቭስ በ17 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።
ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ20ኛ ጊዜ ነው።
ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 19 ጨዋታዎች ሁለቱም በተመሳሳይ ዘጠኝ ጊዜ አሸንፈዋል። በቀሪው አንድ ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል።
ባለፉት አምስት የሊግ ግንኙነታቸው ዌስትሃም በሶስቱ ሲያሸንፍ ፤ዎልቭስ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ድል ቀንቶታል።
ቡድኖቹ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በ20ኛ ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ዎልቭስ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
የዛሬው ጨዋታ ላለመውረድ እየታጋሉ ለሚገኙት ለሁለቱ ቡድኖች እጅጉን ወሳኝ ነው።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት እስከ ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።