ቀጥታ፡

የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን ያረጋገጡበት ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡-የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን በተግባር ያረጋገጡበት ነው ሲሉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን የጎበኙ የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባዔ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡

16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ተሳታፊዎች ዛሬ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ጎብኝተዋል፡፡

ከጎብኚዎቹ መካከል ጅቡቲያዊው ኢሳም አብዱልሃኪም፤ በመጀመሪያ የሰው ልጅ መገኛ ወደ ሆነችው ታሪካዊት አገር ኢትዮጵያ በመምጣቴ እጅግ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በጣም በርካታ ታሪኮችን የያዘ ሆኖ ማግኘታቸውን አመልክተው፤ በዚህም እጅግ መደነቃቸውን ተናግረዋል።

ታሪኩ ኢትዮጵያዊያን ከተባበሩ ለማንኛውም ፈተና የማይበገሩ ህዝቦች መሆናቸውን እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል።

ዛንቢያዊቷ መሲ ችሉ በበኩላቸው፤  የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ከተባበርን ከጦርነት ባሸገር በልማትም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል የሚያረጋግጥ ነው።

የዓድዋ ድል ትክክለኛ የአመራር ብቃትና የህዝብ ቁርጠኝነት የታየበት የጀግንነት ታሪክ ነው ያሉት ደግሞ ሱዳናዊው እስማዔል አሊ ናቸው፡፡

#Ethiopian_News_Agency  #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም