ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የተፈራረሟቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የሀገራቱን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ ናቸው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የተፈራረሟቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የሀገራቱን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ ናቸው
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የተፈራረሟቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የሀገራቱን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ታድመዋል።
በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በውሃና ኢነርጂ፣ በግብርና ፣ በንግድ ፣ በዲጂታል መታወቂያ እና በቱሪዝም ዘርፎች የተፈረሙት እነዚህ ሁሉን አቀፍ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል።
እነዚህ የመግባቢያ ስምምነቶች የሁለቱን ሀገራት ሰፊ አቅም በመደመር ወደ ብልጽግና ለምናደርገው የጋራ ጉዞ መሠረት የሚጥሉ እንደሆኑም ገልጿል።