ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሳይ ሰለሞን በ91ኛው ደቂቃ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ወላይታ ድቻ በ31 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል።
በሊጉም ስድስተኛ ድሉን አስመዘግቧል።
በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ29 ነጥብ ከነበረበት 15ኛ ደረጃ ወደ 17ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ገብቷል።
ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን፣ ሀዲያ ሆሳዕና አርባምንጭ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን አንድ አቻ ተለያይተዋል።