ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ዛሬ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሁለትዮሽ ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበር ገልጸዋል።
በቆይታችን ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ለማጠናከር ያለሙ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ አከናውነናል ብለዋል።
እነዚህ ውይይቶች እና የተፈረሙት ስምምነቶች ለሁለቱም ሀገራት የበለጸገ እና የተባበረ መጻኢ ዕድልን የሚያረጋግጡ፣ የቆዩ ግንኙነቶቻችንን ወደ ተጨባጭ ትብብር ለመቀየር እንደ ወሳኝ መሠረት የሚያገለግሉ የጋራ ቁርጠኝነታችን ማሳያ ጭምር ናቸው ብለዋል።