ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋሩ
አሶሳ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለበዓል የሚሆን ዱቄት፣ ዘይትና ሌሎች ምግብ ነክ ቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ የትንሣኤ በዓልን የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመርዳት እና በመተሳሰብ ማሳለፍ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወቅቱ የመረዳዳት ባህላችንን የበለጠ ማጠናከር እንዳለብን የሚያመላክት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በዓሉን ሁሉም በደስታ እንዲያሳልፍ እንደዚህ አይነት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል።