ቀጥታ፡

የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየምን ጉበኙ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፡- የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየምን ጉብኝተዋል።


 

የቡሩንዲው ፕሬዝደንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው አካል በሆነው በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚየም ጉብኝት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገልጿል።


 

በታላቁ ቤተ-መንግስት ጣሪያ ስር የተገናኙት ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት፤ በአፍሪካውያን የተጻፈውን ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ በጋራ መዘከራቸውንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም