የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ - ኢዜአ አማርኛ
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ) ፦ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናቸዋል ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ያኖሩ ሲሆን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ የሆነውን የዓድዋ ድል ታሪክም አስጎብኝተናቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለነበረዎት ቆይታ እያመሰገንኩ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካውያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚኖርዎት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ ብለዋል።