ቀጥታ፡

ሀዲያ ሆሳዕና ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሄኖክ አርፊጮ በ11ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ጎሏን አስቆጥሯል።

ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሀዲያ ሆሳዕና በ32 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።

 

በሊጉ ስምንተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ22 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም