ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንተ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምኞት ደበበ በ67ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።


 

ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ፋሲል ከነማ በ39 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸውን የጨዋታዎች ብዛት ወደ ዘጠኝ አድርሷል።

 

በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ41 ነጥብ ከነበረበት ሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ዝቅ ብሏል። በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።

ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም