ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪቲካ ጅማ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ጎል ነገሌ አርሲ መሪ ሆኗል።
ከእረፍት መልስ ብሩክ በላቸው በ80ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ለኢትዮጵያ መድን አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ የማድረግ እድል አልተጠቀመም።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ29 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
መድን ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።