ቀጥታ፡

የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

ኢትዮጵያና ቡሩንዲ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው።

ሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን በማቋቋም በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።

የቡሩንዲ ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሜዬ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም