ቀጥታ፡

የሀገራዊ ለውጡ ውጤቶችና ትሩፋቶችን የሚዘክር ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው

ድሬደዋ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የሀገራዊ ለውጡን ታላላቅ ውጤቶችና ትሩፋቶችን የሚዘክር ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ነው።

ከማለዳ ጀምሮ በከተማው ዋና ዋና አደባባዮች እየተካሄደ የሚገኘው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ ላይ የአስተዳደሩ የከተማና የገጠር ነዋሪዎች፣ ሠራተኞች፣ ተማሪዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች በዋናነት የተሳተፉበት ነው።


 

የድጋፍ ሰልፉ ለውጡ ከመጣበት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት 8 የለውጥ ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡትን ሁለንተናዊ ስኬቶች ለመዘከርና ዕውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑም ተመላክቷል።

የሰልፉ ተሳታፊዎችም ይሄኑን ዓላማ አጉልተው ባነገቧቸው መፈክሮች ላይ አረጋግጠዋል።

ከመፈክሮች መካከል የጋራ ማንነት ግንባታ ለብሩህ ኢትዮጵያችን፤ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት፤ መጋቢት 24 የድሬዳዋን ልዕልና አረጋግጧል  የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም