በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ በሀገራዊ ለውጡ ለተመዘገቡ የልማት ድሎች ዕውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ በሀገራዊ ለውጡ ለተመዘገቡ የልማት ድሎች ዕውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ሰመራ፣ሚያዝያ 1/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ በሀገራዊ ለውጡ ለተመዘገቡ የልማት ድሎች ዕውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የድጋፍ ሰልፉ ሐገራዊ ለውጡ ዕውን የሆነበትን የመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የለውጥ ፍሬዎች የሚዘክር እንዲሁም ባለፉት ስምንት ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ድሎችን ዕውቅና የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የኢትዮጵያ ከፍታ በእጃችን ነው፤መጋቢት የፅናት መለኪያ የፈተና መሻገሪያ፤ መሰረት ባለው እርምጃ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች በሰልፈኞቹ እየተላለፉ ነው።