ቀጥታ፡

ፒኤስጂ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በፓርክ ደ ፕሪንስ በተካሄደው ጨዋታ ፒኤስጂ ሊቨርፑልን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ዴዚሬ ዱዌ እና ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

 

በግጥሚያው ከፍተኛ ብልጫ የወሰደው ፒኤስጂ ተጨማሪ ጎሎችን ማስቆጠር የሚችልባቸውን እድሎች አልተጠቀመም።

ሊቨርፑል በጨዋታው ምንም አይነት ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻለም። ቀያዮቹ ደካማ እንቅስቃሴ አድርገዋል።

የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ፒኤስጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ እድሉን አስፍቷል።

በካምፕ ኑ  ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ ባርሴሎናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

 

ሁሊያን አልቫሬዝ እና አሌክሳንደር ሶርሎዝ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

አልቫሬዝ በዘንድሮ የውድድር ዓመት በሻምፒዮንስ ሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ዘጠኝ አድርሷል።

የባርሴሎናው ተከላካይ ፓው ኩባርሲ በ44ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ የጨዋታው ቁልፍ ክስተት ነበር።

የተጫዋች ብልጫው አትሌቲኮ ማድሪድን በሚገባ ጠቅሟል።

ባርሴሎና በሁለተኛው አጋማሽ ግብ ለማስቆጠር ቢጥርም ሊሳካለት አልቻለም።

 

አትሌቲኮ ማድሪድ ከሜዳው ውጪ ወሳኝ ድል የተቀዳጀ ሲሆን ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ እድሉን አስፍቷል።

የሩብ ፍጻሜ መልስ ጨዋታዎች ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም