ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ምድረ ገነት ሽሬን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ ኑር ናስር በመጀመሪያ አጋማሽ ጭማሪ ደቂቃዎች ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ድሬዳዋ ከተማ በ32 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ ሰባተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ምድረ ገነት ሽሬ በ28 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።
በተያያዘም ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ26ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀሌ 70 እንደርታን 3 ለ 0 አሸንፈዋል።
ኢትዮጵያ እና ሸገር ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።