ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመመራት ተነስቶ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታ በተካሄደው ጨዋታ በፍቃዱ አስረሳኸኝ በ10ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ግብ ኢትዮ ኤሌክትሪክን መሪ አድርጓል።
ከእረፍት መልስ ተገኑ ተሾመ በ53ኛው እና ፍጹም ጥላሁን በ76ኛው ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊ ሆኗል።
የኢትዮ ኤሌክትሪኩ ቢኒያም በቀለ በ93ኛው ደቂቃ በቀጥታ በቀይ ካርድ ወጥቷል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ31 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 12ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በውድድር ዓመቱ ያስመዘገባቸው ድሎች ብዛት ስምንት ደርሰዋል።
በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ38 ነጥብ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።