ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋሩ
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናውነዋል።
ፕሬዝዳንቱ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማዕድ ማጋራት በፈጣሪ ዘንድ የተወደደ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅመ ደካማ ወገኖች በበዓላት ወቅት በራቸውን ዘግተው ማሳለፍ የለባቸውም በሚል የጀመሩት ተነሳሽነት ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባህል ይበልጥ እንዲዳብር ማድረጉን ጠቅሰዋል።
ይህ የመረዳዳት ተግባር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በበዓል ወቅት ቤታቸው ባዶ እንዳይሆንና ከሌላው ወገኖች ጋር በጋራ እንዲያሳልፉ የሚያስችል መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
የመንግስት ዋነኛ ዓላማ ሁሉም ዜጋ ራሱን ችሎ የተሻለ ህይወት እንዲመራ ማስቻል መሆኑን ያመለከቱት ፕሬዝዳንቱ፤ ለዚህም መንግስት በሰው ተኮር ፖሊሲው በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።