ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀሌ 70 እንደርታን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ናትናኤል ዳንኤል ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሁዘይፋ ሻፊ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ34 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ በ23 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቡድኑ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።