ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሚር አብዶ በ42ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ሸገር ከተማ መሪ ሆኗል።
ከእረፍት መልስ አቡበከር አዳሙ በ68ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ አድርጋለች።
የሸገር ከተማው የአማካይ ተጫዋች ገዛኸኝ ደሳለኝ በ66ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
በጨዋታው ላይ ኢትዮጵያ ቡና ያገኘውን የቁጥር ብልጫ ተጠቅሞ ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ31 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም።
አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኢትዮጵያ ቡና በ36 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡናማዎቾ ሶስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ማስመዝገብ አልቻሉም።