ቀጥታ፡

ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ ነው

አሶሳ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ዑራ ወረዳ የችግኝ ጣቢያዎች በመገኘት ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ዝግጅትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


 

ከጉብኝቱ በኋላ ባደረጉት ንግግርም በክልሉ ብሎም እንደ ሀገር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

የልማት ስራው ዘንድሮም ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተው ለዚህም በክልሉ በቂ የችግኝ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።


 

ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን በጉብኝታችን አረጋግጠናል ብለዋል።

ከዚህ ፊት የተተከሉ ችግኞች ያሉበትን ደረጃ እና በወረዳው በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችንም ርእሰ መስተዳድሩ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም