ኢትዮጵያ ዩራጓይን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ዩራጓይን አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30 /2018 (ኢዜአ)፦ የ"UEFA Frendship Cup" ውድድር የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዩራጓይ አቻውን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ዛሬ ረፋድ ላይ በቱርኪዬ ሪቫ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ህድአት ካሡ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።
በጨዋታው ኢትዮጵያ ብልጫ ወስዳለች።
በምድብ ሁለት የምትገኘው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች።
በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ሚያዚያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከኮስታሪካ ጋር ያደርጋል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ባዘጋጀው የ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ስምንት ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛል።
የወዳጅነት ስፖርታዊ ሁነቱ ከውድድር ባለፈ በአህጉራት መካከል ያለውን የእግር ኳስ ልማት ትብብርን ማጠናከር እና የልምድ ልውውጥ ማድረግን ያለመ ነው።
ውድድሩ እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።