ከተሞችን ምቹ ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥባቸው የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል-አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ከተሞችን ምቹ ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥባቸው የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል-አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር)
ባሕር ዳር፤መጋቢት 30/2018(ኢዜአ)፦ከተሞችን ለመኖሪያ ምቹ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥባቸው የማድረግ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የአማራ ክልል የከተማ ዘርፍ ተቋማት የ2018 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር)፤ ከተሞችን ምቹ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥባቸው የማድረግ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
የ25 ዓመታት አሻጋሪና ዘላቂ የልማት ዕቅድ ታቅዶ ወደ ሥራ በመገባቱ በበጀት አመቱ ጥሩ አፈፃፀም መታየቱን ገልጸው፤ በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በከተሞች የኮሪደር ልማት ከውበትም ባሻገር የዘመናዊ ከተሞችን ግንባታ መሰረት እያኖረ መሆኑን አንስተው፤ ምቹ ፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ስማርት ከተሞችን የመገንባት ስራ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።