ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሌ/ጄ ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት አራዘሙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሌ/ጄ ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት አራዘሙ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት አራዝመዋል፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 62(9) እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደርን በርዕሰ መስተዳድርነት እንዲመሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ በጸደቀው ደንብ ቁጥር 479/2013 አንቀጽ 4(2) እና የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡት መሠረት ነው የሹመት ጊዜያቸው የተራዘመው።