በተጠባቂው ጨዋታ ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በበርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሉዊስ ዲያዝ እና ሃሪ ኬን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኬን በአጠቃላይ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት 49 አድርሷል።
ኪሊያን ምባፔ ለማድሪድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው ባየር ሙኒክ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።
ባለሜዳው ሪያል ማድሪድ በጨዋታው ላይ ያገኛቸውን የግብ እድሎች ተጠቅሞ ተጨማሪ ጎል ማስቆጠር አልቻለም።
የጀርመኑ ክለብ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ሪያል ማድሪድን ማሸነፍ ችሏል። በሩብ ፍጻሜ ወሳኝ ድል አሳክቷል።
የመልሱ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።
በጆሴ አልቫሌዴ ስታዲየም በተካሄደው የሩብ ፍጻሜ ሌላኛው መርሐ ግብር አርሰናል ስፖርቲንግ ሊዝበንን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ካይ ሃቫርትዝ በ91ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
መድፈኞቹ ከሜዳቸው ውጪ ወሳኝ ድል አግኝተዋል።
የመልስ ጨዋታዎች ሚያዚያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።