ቀጥታ፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሃገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት የሚዘክር የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2018(ኢዜአ) ፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሃገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት የሚዘክር የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ ሀገራዊ ለውጡ ከመጣበት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ አንጸባራቂ ስኬቶችን ለመዘከርና ዕውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።


 

በክልሉ ወላይታ ሶዶ ፣ አርባምንጭና ሌሎችም ከተሞች ከማለዳው ጀምሮ የወጡት ሰልፈኞች “የጋራ ማንነት ግንባታ ለብሩህ ኢትዮጵያችን” ፤ “ቀጣዩ ጀግንነታችን ለኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታችን” ፤ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት” የሚሉ መልዕክቶችን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

በተጨማሪም “ስልጣንን በአፈሙዝ ለመጨበጥ ማሰብ ጊዜው ያለፈበት ነው”፣ “የጋራ ግባችን አፍሪካዊ ተምሳሌትነታችን”፣ “ሰላማችን በእጃችን” የሚሉና ሌሎችም መልዕክቶች ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም