ቀጥታ፡

የአውሮፓ ኃያላኑን ሪያል ማድሪድ እና ባየር ሙኒክን ያገናኘው ተጠባቂ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል። 

ምሽት አራት ሰዓት 84 ሺህ በሚያስተናግደው በርናባው ስታዲየም ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ ስቧል።

በሩብ ፍጻሜው ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ሲቲን፣ ባየር ሙኒክ አትላንታን አሸንፈዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በሻምፒዮንስ ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ29ኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 28 ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ 13 ጊዜ ሲያሸንፍ ባየር ሙኒክ በ11ዱ ድል ቀንቶታል። በቀሪ አራት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

በጨዋታዎቹ ላይ ሪያል ማድሪድ 45 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ፣ ባየር ሙኒክ 42 ጎሎችን አስቆጥሯል።

ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ የተገናኙት እ.አ.አ 2023/24 የውድድር ዓመት ነው። 

በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ በደርሶ መልስ ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፏል። ማድሪድ በፍጻሜው ቦሩሲያ ዶርትሙንድን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።

የጀርመኑ ባየር ሙኒክ ለመጨረሻ ጊዜ ሪያል ማድሪድን ያሸነፈው እ.አ.አ 2011/12 የውድድር ዓመት ነው።

ሁለቱ የአውሮፓ ቁንጮ ክለቦች በአህጉራዊው መድረክ ስኬታማ የሚባሉ ቡድኖች ናቸው።

ሪያል ማድሪድ 15 ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት የውድድሩ ስኬታማ እና ኃያል ክለብ ነው።

ባየር ሙኒክ ስድስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አንስቷል። 

በዛሬው እና በመልሱ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ጠንካራ ፍልሚያ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ስፖርቲንግ ሊዝበን ከአርሰናል በጆሴ አልቫላዴ ስታዲየም ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን በጥሎ ማለፉ ቦዶ ግሊምትን በድምር ውጤት 5 ለ 3 በማሸነፍ ስምንት ውስጥ ገብቷል። 

ስፖርቲንግ በጥሎ ማለፉ በመጀመሪያው ዙር ያጋጠመውን የ3 ለ 0 ውጤት ቀልብሶ ማለፉ አድናቆት አስችሮታል።

በዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው አርሰናል በጥሎ ማለፉ የጀርመኑ ባየር ሌቨርኩሰንን በድምር ውጤት 3 ለ 1 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜው አልፈዋል። 

አርሰናል ዘንድሮ በሻምፒዮንስ ሊጉ ሽንፈት ያላስተናገደ ብቸኛው ክለብ ነው። 

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በውድድሩ ላይ አራት ጊዜ ተገናኝተዋል። አርሰናል አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

በጨዋታዎቹ ላይ አርሰናል አራት ግቦችን ሲያስቆጥር ስፖርቲንግ ሊዝበን ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

እ.አ.አ በ2022/23 በጥሎ ማለፉ ተገናኝተው አርሰናል በደርሶ መልስ ውጤት በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ ማለፉ የሚታወስ ነው።

ቡድኖቹ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አንስተው አያውቁም።

የአርሰናል አጥቂ ቪክቶር ዮኮሬስ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም