የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሚያዚያ 16 ወደ ውድድር ይመለሳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሚያዚያ 16 ወደ ውድድር ይመለሳል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ዳግም ወደ ውድድር እንደሚመለስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ፕሪሚየር ሊጉ በኢትዮጵያ ከ17 እና ከ18 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች የውድድር ተሳትፎ ምክንያት መቋረጡ ይታወቃል።
ከ21ኛው ሳምንት በኋላ የተቋረጠው ፕሪምየር ሊጉ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚቀጥል ፌዴሬሽኑ አመልክቷል።