ዓለም አቀፍ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
ዓለም አቀፍ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር (One day meeting ) ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ስታዲየም መሮጫ ትራክ እድሳት ተጠናቆ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አመልክቷል።
ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር (One Day Meeting) በአዲስ አበባ ስቴዲየም እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል።
ውድድሩ ከተለያዩ ሀገሮች የተውጣጡ አትሌቶች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ ሽልማት ያገኛሉ።
የአንድ ቀን ውድድሩ የዓለም አትሌቲክስ ዓመታዊ የኢንተርኮንቲነንታል ውድድር አካል ነው።