ቀጥታ፡

በሐረሪ ክልል በሀገራዊ ለውጡ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፤መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ሀገራዊ ለውጡ እውን መሆን የጀመረበትን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ በሐረሪ ክልል የሚገኙ የከተማና የገጠር ወረዳዎች ነዋሪዎች የተሳተፉበት የድጋፍ ሰልፍ በኢማም አህመድ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።

በስታዲየሙ የተገኙ ተሳታፊዎች የለውጡን ጉዞ የሚደግፉና ለቀጣይ ስኬቶች ያላቸውን ዝግጁነት የሚገልጹ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።


 

ከተደመጡት መፈክሮች መካከልም ፦

👉"ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!"

👉 "እሳቤያችን ዘመን ተሻጋሪ፣ ተግባራችን ትውልድ ቀያሪ!"

👉" ሐረርን ከቀደምት ከተማነት ወደ ብልፅግና ተምሳሌትነት እናሸጋግራለን!" የሚሉ ይገኙበታል።


 

ሰልፈኞቹ መጋቢት 24 በኢትዮጵያ እውነተኛ የዲሞክራሲ ግንባታ የተረጋገጠበትና ሀገሪቱን የማላቅ ጉዞ የተጀመረበት ቀን መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም