ቀጥታ፡

የለውጡን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ቦንጋ፤ መጋቢት 28/2018 (ኢዜአ)፦ የሀገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

የድጋፍ ሰልፍ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎችንና ስኬቶችን በመደገፍ ቀጣይነት እንዲኖራቸው መልእክቶች እየተላለፉበት ይገኛል። 


 

“የመጋቢት 24 ለውጥ ለአዲሱ ትውልድ ተስፋ ለሀገራችን አዲስ ተስፋ ”፣ የመጋቢት 24  የኢትዮጵያ ብልፅግና ጉዞ የተጀመረበት ታሪካዊ ቀን”፣ "ባለፉት ዓመታት በፈተናዎች ውስጥ የጸናች በስኬቶች የደመቀች ኢትዮጵያን ገንብተናል" የሚሉ እና ሌሎችም መልዕክቶች በድጋፍ ሰልፉ ላይ እየተላለፉ ነው። 


 

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የከተማው ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም