ቀጥታ፡

በኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ ማንችስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን  ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኤፍኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማምሻውን በዌስትሃም ዩናይትድ ለንደን ስታዲየም ተደርጓል።

በዚሁ መሰረት ማንችስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን እና ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ በግማሽ ፍጻሜው ይገናኛሉ።

የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ሚያዚያ 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳሉ።

154 ዓመታትን ያስቆጠረው ኤፍኤ ካፕ የዓለማችን አንጋፋው የእግር ኳስ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም