ሊድስ ዩናይትድ ከ39 ዓመታት በኋላ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሊድስ ዩናይትድ ከ39 ዓመታት በኋላ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የመጨረሻ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን በመለያ ምት አሸንፏል።
ማምሻውን በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዎ ታናካ በ26ኛው ደቂቃ በጨዋታ እና ዶምኒክ ካልቨርት-ልዊን በ75ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ያስቆጠሯቸው ግቦች ሊድስ ዩናይትድን መሪ አድርጓል።
ጨዋታው በሊድስ ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ሲባል ማቴውስ ፈርናንዴዝ በ93ኛው እና አክሴል ዲሳሲ በ96ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ዌስትሃም ዩናይትድ አቻ ሆኗል።
ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በመጠናቀቁ 30 ደቂቃ ተጨምሯል።
በጭማሪ ሰዓት አሸናፊው ባለመለየቱ ምክንያት ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።
በዚሁ መሰረት ሊድስ ዩናይትድ 4 ለ 2 በማሸነፍ ከ39 ዓመታት በኋላ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ አልፏል።
ዌስትሃም ዩናይትድ ዩናይትድ ከ35 ዓመታት በኋላ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ ህልሙ አልተሳካም።
ጨዋታውን ተከትሎ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ተጠናቋል።
ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ዌስትሃም ዩናይትድ እና ሳውዝሃምፕተን ለግማሽ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው።