ቀጥታ፡

ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የተገናኙት ሀዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 2 አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው የተካሄደው 10 ሠዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ነው።


 

በዚሁ ጨዋታም ያሬድ ብሩክ እና ሽመልስ በቀለ ለሐዋሳ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

እንዲሁም ነጻነት ገ/መድኅን እና ዳዊት ገብሩ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።


 

ቀደም ብሎ 9 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ነጌሌ አርሲ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም