ነጌሌ አርሲ አዳማ ከተማን አሸንፏል - ኢዜአ አማርኛ
ነጌሌ አርሲ አዳማ ከተማን አሸንፏል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ነጌሌ አርሲ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል።
9 ሠዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ ሁለቱም እስከ እረፍት ድረስ ያለምንም ግብ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከእረፍት መልስ ዳዊት ተፈራ እና ሮሆቦት ሰላሎ ለነጌሌ አርሲ እንዲሁም ዳዋ ሁቴሳ ለአዳማ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎም ነጌሌ አርሲ በ41 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም አዳማ ከተማ በ33 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።