ማንችስተር ሲቲ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ ሁለት በጨዋታ እና አንድ በፍጹም ቅጣት ምት ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።
አንቶዋን ሴሜኒዮ ቀሪዋን ጎል ለሲቲ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የሊቨርፑሉ መሐመድ ሳላህ በ64ኛው ደቂቃ ቡድኑ ያገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ያገኛቸውን የግብ እድሎች በሚገባ መጠቀሙ አሐናፊ አድርጎታል።
ውጤቱን ተከትሎ የሰባት ጊዜ የኤፍኤ ካፕ አሸናፊው ማንችስተር ሲቲ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፏል።
የስምንት ጊዜ የዋንጫ ባለቤቱ ሊቨርፑል የዘንድሮ ጉዞው ሩብ ፍጻሜ ላይ ተገቷል።