ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያብስራ ጎሳዬ በመጀመሪያው አጋማሽ ማብቂያ ባስቆጠረው ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪ መሆን ችሏል።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ያብስራ ጎሳዬ በ63ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ባስቆጠረው ግብ ሀዲያ ሆሳዕና አቻ ሆኗል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል ፉዓድ አብደላ በ93ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስገኝቷል።

ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ28 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ወደ 15ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። 

በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና በ29 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም