ምድረ ገነት ሽሬ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
ምድረ ገነት ሽሬ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል እና ምድረ ገነት ሽሬ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዓለምብርሃን ይግዛው በ50ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል መቻል መሪ ሆኗል።
ተካልኝ ዳኜ በ77ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ለምድረ ገነት ሽሬ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
ጨዋታውን ተከትሎ መቻል በ37 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ምድረ ገነት ሽሬ በ28 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 15ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ድል ማስመዝገብ አልቻለም።
ዛሬ ቀን ላይ በተካሄዱ ጨዋታዎች በሊጉ ግርጌ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ሸገር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከባህር ዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ከፋሲል ከነማ ያደረጓቸው ጨዋታዎች ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።