ቀጥታ፡

የመውረድ ስጋት ያለበት አርባምንጭ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት አርባምንጭ ከተማ ሸገር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሴኔጋላዊው ማማዱ ሴክ እና የሸገር ከተማው ገዛኸኝ ደሳለኝ በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ቢንያም ፍቅሩ ለሸገር ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው አርባምንጭ ከተማ በ22 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል። 

ቡድኑ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።  19ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው መቀሌ 70 እንደርታ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነትም ወደ አንድ ዝቅ አድርጓል። 

ከሁለት ተከታታይ ድሎች በኋላ የተሸነፈው ሸገር ከተማ በ30 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። 

አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በውድድር ዓመቱ ያስተናገዳቸው ሽንፈቶች ብዛት ሰባት ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም