በአማራ ክልል 1 ሺህ 224 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ተወሰነ - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል 1 ሺህ 224 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ተወሰነ
ባህር ዳር፤መጋቢት 25/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል 1 ሺህ 224 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ በይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑት ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የባህሪ ለውጥ ያመጡና የይቅርታ መመሪያውን ያሟሉ ናቸው ብለዋል።
በተጨማሪም እርቅና ካሳ የፈፀሙ፣ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ታንፀው መልካም ስነ- ምግባር ያሳዩ የሚገኙበት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት 1 ሺህ 224 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የወንጀልን አስከፊነት ከማስተማር ባለፈ የበደሉትን ለመካስና የልማት አርበኛ እና የሰላም አምባሳደር ሆነው ለማገልገል መዘጋጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።