ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ እና ድል አሁንም አልተገናኙም  

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።

ጨዋታው በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተከናውኗል።

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ36 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ከድል ርቋል።

ድሬዳዋ ከተማ በ29 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም