ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ባህር ዳር ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ባህር ዳር ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው የተካሄደው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ነው።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ38 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ አልቻለም።

ባህር ዳር ከተማ በ32 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ስምንተኛ ከፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም