የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ - ኢዜአ አማርኛ
የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ
አዲስ አበባ፤መጋቢት 25/2018(ኢዜአ)፦የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት ያጠናቀሩትን አጀንዳ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት የመጀመሪያ ዙር ከመጋቢት 23 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሲያካሂድ ቆይቷል።
በዛሬው እለትም የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት የመጀመሪያው ዙር አጀንዳ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
በዚህም የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት ያጠናቀሩትን አጀንዳ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች የተጠናቀረውን አጀንዳ ተረክበዋል።