ቀጥታ፡

የ25ኛ ሳምንት የአዲስ አበባ ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦  በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊካሄዱ የነበሩ የ25ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም መዘዋወራቸውን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።

ከ25ኛ እስከ 28ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንዲካሄዱ መርሐ ግብር መውጣቱ ይታወቃል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማካሄድ ቀደም ብሎ ፕሮግራም የተያዘለት የ25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የስታዲየሙ የትራክ ስራ ባለማለቁ ምክንያት ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም መዘዋወሩን ማህበሩ ገልጿል። 

ከ26ኛ ሳምንት በኋላ ያለው መርሃ ግብር እና የመጫወቻ ሜዳ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም