በለውጡ የተለወጠችው ሀረር ከተማ! - ኢዜአ አማርኛ
በለውጡ የተለወጠችው ሀረር ከተማ!
መጋቢት 24 በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን የከፈተ የለውጥ ምዕራፍ ጅማሮ ማብሰሪያ ነው።
ለውጡም በፈተናዎች ውስጥ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚያሻግሩ ስኬቶችን በማስመዝገብ ዘልቋል፡፡
በዚህ ለውጥም የኢትዮጵያን ስብራቶች የማከም ጉዞ ሀረር ከተማ ቀዳሚ ተጠቃሚና የለውጡ ተጨባጭ ፍሬ ማሳያ ነች፡፡
ከተማዋ በታሪኳ አይታው በማታውቅ ፍጥነት ከፍታዋን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ለውጦችን እያስመዘገበች ትገኛለች።
ሀረረ እንደ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማነቷ ታሪኳን በሚመጥን ደረጃ ሳታድግ የቆየች ብትሆንም ከለውጡ ወዲህ ግን ይህ ታሪክ እጅጉን ተቀይሯል።
አደጋ ተጋርጦበት የነበረው አለም አቀፉ የጀጎል ቅርስ ከአደጋ መታደግ የተቻለው በእነዚህ የለውጥ ዓመታት ነው።
አባዲር ፕላዛና ኑር ፕላዛን ጨምሮ በከተማው እና በጀጎል መልሶ ማልማት የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማዋ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን ከማሳደግ ባለፈ ለነዋሪዎች የተመቸች እንድትሆን አስችሏታል፡፡
በከተማዋ በኮሪደር ልማት ከተሰሩ መካከል ሰፋፊ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራቶች የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የመዝናኛ ስፍራዎች ተጠቃሾች ናቸው።
በተሰሩ ሁሉን አቀፍ ስራዎችም ሀረር ዛሬ ላይ ለመጎብኘት የምታጓጓ ከተማ ሆናለች።